ቀጥታ፡

ኢኒስቲትዩቱ በሀገር ውስጥ የጥራት መሰረተ ልማት ላይ በትኩረት እየሰራ ነው

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሥነልክ ኢኒስቲትዩት በሀገር ውስጥ የጥራት መሰረተ ልማት ላይ በትኩረት እየሰራ  መሆኑን  አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ሥነ ልክ ኢኒስቲትዩት አለም አቀፍ የሥነ ልክ ቀንን "ለነገ ዘላቂነት ዛሬ እንለካለን" በሚል መሪ ቃል አክብሯል።


 

የኢትዮጵያ ሥነ ልክ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሙሉጌታ ደርበው(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለፁት ፤ኢንስቲትዩቱ በሀገር ውስጥ የጥራት መሰረተ ልማት ላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡

ኢኒስቲትዩቱ የሥነ ልክ ላብራቶሪዎች በዘመናዊ መንገድ እንዲሰሩ አዳዲስ የአለካክ ዘዴዎችን በመፍጠር የልኬት ሳይንስን እየተገበረ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የአሀዶች ስርአትን በማስተዋወቅና ሌሎች ተቀባይነት ያላቸውን የልኬት መስፈሪያዎች ዘመናዊ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢኒስቲቲዩቱ ኢትዮጵያ መለካት ትችላለች የሚለውን እሳቤ ለማሳካት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች ከደረጃ በታች እንዳይሆኑ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ጥራቸውን የጠበቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ብሔራዊ የሥነ ልክ ኢንስቲቲዩት ሀገራዊ የልኬት ደረጃ ተዋረድን የመጠበቅ ኃላፊነት ተጥሎበታል።

በተጨማሪም የካሊብሬሽን ፣በጤና ፣ በግንባታ ፣በኢንዱስትሪ ፣ በኤሌክትሪክና በሌሎች የሳይንስ መሳሪያዎችን የጥራት ደረጃ ከመፈተሽ በተጓዳኝ የጥገና አገልግሎትም ይሰጣል።

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም