ኢትዮጵያና ኩዌት የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያና ኩዌት የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያና ኩዌት በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና በኢትዮጵያ የኩዌት አምባሳደር ናይፍ ሃኘስ አል ኦይታይቢ ፈርመውታል።
በመግባቢያ ስምምነቱ ላይ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሠለሞን ሶካ እና ዳንኤል ተሬሳ፣ በኩዌት የኢትዮጵያ አምባሳደር ሰኢድ ሙሁመድ፣ በኢትዮጵያ የኩዌት አምባሳደር ናይፍ ሃኘስ አል ኦይታይቢን ጨምሮ የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ስምምነቱ ወደ ኩዌት የሥራ ስምሪት የሚያደርጉ ኢትዮጵያውያን መብትና ጥቅማቸው ተጠብቆ ህጋዊ የስራ ዕድል የሚያገኙበትን የትብብር ሁኔታ ለመፍጠር ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው ተገልጿል።