ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና በተካሄደው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይ ሲ ቲ ፍጻሜ ውድድር አሸነፉ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 19/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በቻይና በተካሄደው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ የአይ ሲ ቲ ፍጻሜ ውድድር ሶስተኛውን ሽልማት አሸነፉ።

ኢትዮጵያን ወክለው የሁዋዌ ዓለም አቀፍ አይ ሲ ቲ ውድድርን በቻይና ሼንዘን ከተማ በኮምፒውቲንግ ትራክ የተሳተፉት 3 ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ሶሰተኛውን ሽልማት ከማሌዢይ፣ ሜከሲኮ እና ኬንያ ቡደን ጋር መጋራታቸው ተጠቁሟል።

ውድድሩ ከግንቦት 14 እስከ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ከመላው ዓለም የተውጣጡ ተማሪዎች በተሳትፉበት በሶስት የውድድር ትራኮች (Innovation, Network and Computing) ተካፋፍሎ የተካሄደ መሆኑም ተገልጿል።


 

የኢትዮጵያ ቡድን የተወከለው ከአርባ ምንጭና ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በተገኙ ተማሪዎች መሆኑን አመላክቶ በኮምፒውቲንግ ትራክ ውድድር ሶስተኛውን ሽልማት አሸንፎ ዛሬ ወደ ሀገሩ መመለሱም ተጠቁሟል።

ትምህርት ሚኒስቴር በተማሪዎቹ ውጤት የተሰማውን ደስታም በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ ገልጿል።

ወደፊትም የተማሪዎችን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት እድል የሚፈጥሩ ውድድሮች ላይ ያለውን ተሳትፎ ለማሳደግ ከመሰል ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች ጋር መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም