አርባ ምንጭ ከተማ የከፍተኛ ሊግ አሸናፊ ሆነ - ኢዜአ አማርኛ
አርባ ምንጭ ከተማ የከፍተኛ ሊግ አሸናፊ ሆነ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 18/2016(ኢዜአ)፦ አርባ ምንጭ ከተማ ኢትዮ ኤሌክትሪክን 1 ለ 0 በማሸነፍ የ2016 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ አሸናፊ ሆኗል።
የዘንድሮው የከፍተኛ ሊግ ውድድር ዛሬ ፍጻሜውን አግኝቷል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ አህመድ ሁሴን ለአርባ ምንጭ ከተማ የማሸነፊያዋን ግብ በፍጹም ቅጣት ምት አስቆጥሯል።
አርባ ምንጭ ከተማና ኢትዮ ኤሌክትሪክ በከፍተኛ ሊግ በየምድባቸው በመሪነት በማጠናቀቅ ወደ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ማደጋቸው የሚታወስ ነው።