ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ቡና ሀምበርቾን 6 ለ 1 አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 18/2016(ኢዜአ)፦ በ26ኛው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ሀምበርቾን 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈ።

የኢትዮጵያ ቡናን ጎሎች መሐመድ ኑር ናስር ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር፤ አማኑኤል ዮሐንስ በፍጹም ቅጣት ምት፣ አማኑኤል አድማሱ፣ ጫላ ተሺታና የሀምበርቾው ግብ ጠባቂ ምንታምር መለሰ በራሱ ግብ ላይ ቀሪዎቹን ግቦች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

አላዛር አድማሱ ለሀምበርቾ ብቸኛዋን ጎል አስቆጥሯል።

ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ ሦስተኛ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበ ሲሆን በ44 ነጥብ ከነበረበት 5ኛ ደረጃ ወደ 4ኛ ከፍ ብሏል።

ሀምበርቾ በሊጉ 20ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደ ሲሆን በ8 ነጥብ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ሀምበርቾ በሊጉ እስካሁን ያሸነፈው 1 ጨዋታ ብቻ ነው። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም