ቀጥታ፡

በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢትዮጵያውያን ኮሙዩኒቲ ማህበር አንድ መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር ቦንድ ገዛ

አዲስ አበባ፤ግንቦት 18 /2016 (ኢዜአ ):-በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢትዮጵያውያን ኮሙዩኒቲ ማህበር አንድ መቶ ሺህ የአሜሪካን ዶላር የቦንድ ግዥ ፈፀመ ። 

በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢትዮጵያውያን ኮሙዩኒቲ ማኅበር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መሠረተ ድንጋይ የተጣለበትን 13ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የ100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ/ የአሜሪካን ዶላር የቦንድ ግዥ ፈፀመ።

በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ቆንሱል ጄነራል  አምባሳደር አክሊሉ ከበደ የቦንድ ግዥ ስነስርዓቱ በተካሄደበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መሠረተ ድንጋይ የተጣለበት 13ኛ ዓመት  እየተከበረ ነው።

በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የሚኖሩ የኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም  ባለፉት 13 ዓመታት ላደረጉት  ሁለንተናዊ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።


 

በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የኢትዮጵያዊያን ኮሙዩኒቲ ማኅበር ሊቀመንበር አቶ እድሪስ ቡንሱሩ በበኩላቸው ማኅበሩ ለፈፀመው የቦንድ ግዥ ከፍተኛ ኩራትና ደስታ የተሰማቸው መሆኑን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያውያን ኮሙዩኒቲ ማኅበር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መሠረተ ድንጋይ ከተጣለበት  እስከአሁኑ  አምስት መቶ ሃምሳ ሺህ የአሜሪካን ዶላር የቦንድ ግዥ  መፈጸማቸውን  ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማህበራዊ ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም