ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አብራሪዎችና ቴክኒሻኖችን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 17/2016(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኢትዮጵያ አየር ኃይል አካዳሚ ያሰለጠናቸውን አብራሪዎችና ቴክኒሻኖች አስመረቀ።

አየር መንገዱ በመጀመሪያው ዙር 140 ሰልጣኞችን ያስመረቀ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለትም 259 አብራሪዎችንና ቴክኒሻኖችን አስመርቋል።


 

አየር መንገዱ በአፍሪካ ቀዳሚ ሊሆን የበቃው ትጋት ባላቸው ሰራተኞቹ ነው ያሉት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፤ አዲስ ተመራቂዎችም ከአየር መንገዱ ሰራተኞች ጠንካራ የስራ ባህልን ሊወርሱ እንደሚገባ ተናግረዋል።


 

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል ይልማ መርዳሳ በበኩላቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት የሚያደርገውን ጥረት የኢትዮጵያ አየር ኃይል እንደሚያግዝ ማረጋገጣቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም