መቻል እና ሻሸመኔ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል - ኢዜአ አማርኛ
መቻል እና ሻሸመኔ ከተማ ነጥብ ተጋርተዋል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 16/2016(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት መርሐ ግብር መቻልና ሻሸመኔ ከተማ ዛሬ ባካሄዱት ጨዋታ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የአጥቂ መስመር ተሰላፊዎቹ ምንይሉ ወንድሙና በረከት ደስታ ለመቻል ግቦቹን አስቆጥረዋል።
የአማካይ ተጫዋቾቹ አብዱልቃድር ናስርና ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ ለሻሸመኔ ከተማ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ውጤቱን ተከትሎ 2ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው መቻል ነጥቡን ወደ 51 ነጥብ ከፍ ያደረገ ሲሆን ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በነጥብ እኩል የመሆን እድሉን ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
በ53 ነጥብ ሊጉን የሚመራው የኢትዮጵያ ባንክ የ26ኛ ሳምንት ጨዋታውን ነገ ከፋሲል ከነማ ጋር ያደርጋል።
ሻሸመኔ ከተማ በ14 ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጣና ውስጥ ይገኛል።
በ26ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባሕርዳር ከተማ ከወላይታ ድቻ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።