ለዲጂታል ምህዳሩ የወጡ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ እና ዲጂታል ቴክኖሎጂ  ዕድገት ጋር መጣጣማቸው እንዲጠና  ምክር ቤቱ አቅጣጫ አስቀመጠ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 16/2016(ኢዜአ)፦ የብሄራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት በዲጂታል ምህዳሩ የወጡ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ እና ዲጂታል ቴክኖሎጂ  ዕድገት ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸው እንዲጠና  አቅጣጫ አስቀምጧል።

ምክር ቤቱ መደበኛ ሁለተኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት ያደረገ  ሲሆን በአንደኛ መደበኛ ስብሰባው ያስቀመጣቸውን አቅጣጫዎች ትግበራ  መገምገሙን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አመልክተዋል ፡፡ 


 

ፓርኩ ያሉበትን ውስን ተግዳሮቶች በመፍታት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ እና ከመንግስት ጋር ያለውን ትብብር የሚያጠናክር ቁመና እንዲላበስ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር መስራት እንደሚገባ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል። 

በፓርኩ በዳታ ሴንተር ዘርፍ የተሰማሩ ሁለት ድርጅቶችን እና የኢንኩቤሽን ማዕከልን መጎብኘታቸውንም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።


 

የተመለከትናቸው ድርጅቶች በዘርፉ ለተሰማሩ አካላት አስፈላጊውን መሰረተ ልማት አሟልተው ዝግጅት ከማጠናቀቃቸውም በላይ ለደንበኞቻቸው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ተመልክተናል ብለዋል። 

በአጠቃላይ በፓርኩ ያየነው የስራ እንቅስቃሴ የዲጂታል 2025 ስትራቴጂን ዕውን ለማድረግ ትልቅ ተቋም እየተገነባ መሆኑን ነው ሲሉም ገልጸዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም