ቀጥታ፡

በየም ዞን ሳጃ ከተማ በ30 ሚሊየን ብር ወጪ ለሚገነባው የግብርና ምርቶች የግብይት ማዕከል የመሠረተ-ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 16/2016(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በየም ዞን ሳጃ ከተማ በ30 ሚሊየን ብር ወጪ ለሚገነባው የግብርና ምርቶች የመንገድ ዳር የግብይት ማዕከል  የመሠረተ-ድንጋይ ተቀመጠ ። 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው ከ37 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ለሚያደርገው የግብይት ማዕከል ግንባታ የመሠረተ-ድንጋይ አስቀምጠዋል ።

የመሠረተ-ድንጋይ በማስቀመጥ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ፋጤ ሰርሞሎ፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የክልሉ የግብርና ቢሮ ኃላፊ ዑስማን ሱሩር፣ የዞን ዋና አስተዳዳሪዎች፣ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ሀገር ሽማግሌዎችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የግብርና ምርቶች የመንገድ ዳር የግብይት ማዕከል ግንባታም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም የገንዘብ ድጋፍ የሚገነባ መሆኑ ተገልጿል። 

የግብይት ማዕከል ግንባታው በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም