አዲስ አበባን ትውልድ የሚገነባባት፣ ለሁለንተናዊ ዕድገትና ብልጽግና የሚተጉ ጥበበኛ ወጣቶችን የምታፈራ ከተማ ለማድረግ የጀመርነው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 16/2016 (ኢዜአ)፦ አዲስ አበባን ትውልድ የሚገነባባት፣ ለሁለንተናዊ ዕድገትና ብልጽግና የሚተጉ ጥበበኛ ወጣቶችን የምታፈራ፣ የሀገራችን የብልጽግና ተምሳሌት ከተማ ለማድረግ የጀመርነው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ “በፈጠራ ስራ የዳበረ ትውልድ ለሁለንተናዊ ዕድገትና ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ ዘጠነኛውን ከተማ አቀፍ የሳይንስና ፈጠራ የተማሪዎች ዓውደ ርዕይ በወዳጅነት አደባባይ መክፈታቸውን አስታውቀዋል።


 

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት እያከናወንናቸው ያሉ ስራዎች ፍሬ እየሰጡ መሆናቸውን በዓውደ ርዕዩ የተመለከትናቸው የተማሪዎች የፈጠራ ስራዎች አስገንዝበውናል ብለዋል።

ለትውልድ ግንባታ የላቀ ትኩረት በመስጠት የተማረውን በተግባር የሚያሳይ ችግር ፈቺ ትውልድ ለመገንባት እና አዲስ አበባን ትውልድ የሚገነባባት፣ ለሁለንተናዊ ዕድገትና ብልጽግና የሚተጉ ጥበበኛ ወጣቶችን የምታፈራ፣ የሀገራችን የብልጽግና ተምሳሌት ከተማ ለማድረግ የጀመርነው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም