ዛሬ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ - ኢዜአ አማርኛ
ዛሬ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ዋለ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 14/2016 (ኢዜአ)፦በዛሬው ዕለት ቀን 9፡30 ሰዓት ገደማ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ተከስቶ የነበረው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ።
እሳቱ የተፈጠረው ከአውሮፕላን ማረፊያው አጥር ውጭ ባሉ የመኖሪያ ቤቶች ውስጥ እንደነበረና አሁን ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉንም ገልጿል።
በአደጋው መከሰት ምክንያት የአየር መንገዱ ዕለታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ምንም ዓይነት መስተጓጎል እንዳልነበረም አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።