አዲስ አበባ እና ሾንግሽንግ የእህትማማች ከተሞች ስምምነትን ተፈራረሙ - ኢዜአ አማርኛ
አዲስ አበባ እና ሾንግሽንግ የእህትማማች ከተሞች ስምምነትን ተፈራረሙ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 14/2016(ኢዜአ)፦ አዲስ አበባ እና የቻይናዋ ሾንግሽንግ ከተማ የእህትማማች ከተሞች ስምምነትን መፈራረማቸው ተገለጸ።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውበትና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ሃላፊ ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ በቻይናዋ በሾንግሽንግ ከተማ የስራ ጉብኝት አካሂዷል።
በዚህም በአዲስ አበባ እና ሾንግሽንግ ከተማ መካከል ያለውን ትብብር የሚያጠናክር የእህትማማች ከተሞች ስምምነት መፈራረማቸውን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
ስምምነቱ የንግድ፣ የትምህርት፣ የባህል ለባህል ትስስርና ሌሎች መስኮችን እንደሚያካትት የተመላከተ ሲሆን በኢትዮጵያና ቻይና መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኙነት እንደሚያጎለብትም ተገልጿል።
በቀጣይም የሁለቱን ሀገራት ጠንካራ ግንኙነት የሚሳያድጉ ተግባራት በትኩረት እንደሚከናወኑ ተገልጿል።