በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ህግን በማስከበር የተገኘው ሰላም ለልማት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የዞኑ ኮማንድ ፖስት ገለጸ - ኢዜአ አማርኛ
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ህግን በማስከበር የተገኘው ሰላም ለልማት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የዞኑ ኮማንድ ፖስት ገለጸ
ደብረብርሀን ፤ ግንቦት 13 /2016 (ኢዜአ) ፡- በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ህግን በማሰከበር የተገኘው ሰላም ለልማትና መልካም አስተዳደር ተግባራት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የዞኑ ኮማንድ ፖስት ገለጸ።
ኮማንድ ፖስቱ ከዞን ፣ ከወረዳና ከደብረብርሀን ከተማ አስተዳደር የአመራር አባላት ጋር የተገኘውን ሰላም አስጠብቆ በማስቀጠልና ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ እየመከረ ነው።
የሰሜን ሸዋ ዞን ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢና የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ምክትል አዛዥ ብርጋዴል ጀነራል አበባው ሰይድ እንደገለጹት፤ አካባቢውን ከፅፈኛው የማጽዳቱ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ።
በአሁኑ ወቅት በሁሉም የዞኑ አካባቢዎች የሰፈነው ሰላም ለልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ተናግረዋል።
የፀጥታ ሀይሉ ህግ ከማስከበር ጎን ለጎን የግብርናው ስራ በተገቢው እንዲከወን የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ በፍትሃዊነት እንዲሰራጭ መደረጉን ጠቅሰዋል።
በየደረጃው የሚገኙ የአመራር አባላት ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ሰላም ሰፍኖ ልማት እንዲቀጥል የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ እንዲያጠናክሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።