ቀጥታ፡

ሀገር አቀፍ የፖሊስ ምርምር ሲምፖዚየም በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 13/2016(ኢዜአ)፦6ኛው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ምርምር ሲምፖዚየም በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀምሯል። 

በመድረኩ በሀገር አቀፉ የፖሊስ ምርምር ሲምፖዚየሙ የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ተፈሪ ጥያሩ፣ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል መስፍን አበበ፣ የሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አለማየሁ ደበበ (ዶ/ር)፣ መከላከያ ሠራዊት አመራሮች፣ የፖሊስ መኮንኖችና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል። 

በሰንዳፋ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ የጀመረው ዓመታዊው የፖሊስ ምርምር ሲምፖዚየም ዛሬ እና ነገ የሚካሄድ ሲሆን ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች የሚነሱበት እንደሚሆን ይጠበቃል።

በድንበር ተሻጋሪ ስደትና በሰዎች መነገድ፣ የግጭት አስተዳደርና ተፈጥሯዊ ሁኔታ፣ የግጭት መነሻና የሠላም ግንባታ ጉዳይ በስፋት የሚመከርበት ይሆናል።

የመንገድ አስተዳደር የትራንስፖርት ደኅንነትና ትራፊክና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ጽሁፎች ቀርበው ምክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም