ቀጥታ፡

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከጣሊያን አቻቸው አድሚራል ጉሴፔ ካቮ ድራገን ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2016(ኢዜአ)፦ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከጣሊያን አቻቸው አድሚራል ጉሴፔ ካቮ ድራገን ጋር ተወያዩ።

በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የተመራው የኢትዮጵያ የመከላከያ ልዑካን ቡድን በጣሊያን ወገን በተደረገለት ግብዣ መሠረት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል።

የልዑካን ቡድኑ በጣሊያን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አድሚራል ጉሴፔ ካቮ ድራገን እና በሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል።

በዛሬው ዕለትም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከጣሊያን አቻቸው አድሚራል ጉሴፔ ካቮ ድራገን ጋር በወታደራዊ ትብብሮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በውይይታቸውም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሁለቱ ሀገራት መካከል እያደገ የመጣውን ግንኙነት አውስተዋል፡፡

ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በጣሊያን ያደረጉት ጉብኝት እና ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በሀገራችን ያደረጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለሀገራቱ ግንኙነት መጠናከር አመላካች መሆኑን መጥቀሳቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም