ቀጥታ፡

በሞሮኮ ማራካሽ በተካሄደ የ5000 ሜትር ሩጫ ውድድር መዲና ኢሳ አሸነፈች

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2016 (ኢዜአ)፦ ሞሮኮ ማራካሽ በተካሄደው የዳይመንድ ሊግ 5000 ሜትር ውድድር መዲና ኢሳ 14 ደቂቃ ከ34 ሰከንድ 16 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት አሸነፈች።

በውድድሩ ፉተን ተስፋዬ 14 ደቂቃ ከ34 ሰከንድ ከ21 ማይክሮ ሰከንድ 2ኛ፣ መልክናት ውዱ 4ኛ፣ ልቅና እንባው 5ኛ፣ ገላ አበሴ 8ኛ እንዲሁም ፍሬህይወት ገሰሰ 10ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ማጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

እንዲሁም በወንዶች 800 ሜትር ሀብታሙ አለሙ 2ኛ፣ በወንዶች 1500 ሜትር ለሜቻ ግርማ 4ኛ፣ ታደሰ ለሚ 7ኛ እንዲሁም ኩማ ግርማ 9ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ማጠናቀቃቸውም ተጠቁሟል።

በ3000 ሜትር መሰናክልም እንዲሁ ጌትነት ዋለ 2ኛ፣ ሳሙኤል ፍሬው 4ኛ እንዲሁም አብርሃም ስሜ 15ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም