ኢትዮጵያ 3ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ስታሸንፍ የቡድኑ አባል የነበሩት ኃ/ማርያም መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ 3ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ስታሸንፍ የቡድኑ አባል የነበሩት ኃ/ማርያም መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦ በ1954 ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ስታሸንፍ የብሔራዊ ቡድኑ ተጫዋች የነበሩት ኃይለማርያም መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡
በስፖርት ቤተሰቡ "ሻሾ" በሚል ቅፅል ስም በስፋት የሚታወቁት ኃይለማርያም መኮንን ከ1940ዎቹ መጨረሻ እስከ 1960ዎቹ መጀመሪያ ድረስ እግር ኳስ ተጫውተዋል፡፡
በተጫዋችነት ዘመናቸውም ለጥቅምት 23፣ ሸዋ ፖሊስ፣ ዳኘው እና ሸዋ ምርጥ መጫወታቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንንም በተለያዩ የዕድሜ ዕርከኖች እና ዋናው ቡድን እንዳገለገሉም እንዲሁ፡፡
በ1954 ኢትዮጵያ ሦስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ስታሸንፍ የቡድኑ አባል እንደነበሩም በመረጃው ተመላክቷል፡፡