በሎስአንጀለስ በተካሄደ የ1 ሺህ 500 ሜትር የሴቶች ሩጫ አትሌት ድርቤ ወልተጂ አሸነፈች - ኢዜአ አማርኛ
በሎስአንጀለስ በተካሄደ የ1 ሺህ 500 ሜትር የሴቶች ሩጫ አትሌት ድርቤ ወልተጂ አሸነፈች
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 11/2016(ኢዜአ)፦ በሎስአንጀለስ በተካሄደ የ1 ሺህ 500 ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድር አትሌት ድርቤ ወልተጂ አሸነፈች።
በሎስአንጀለስ በተካሄደ የ1 ሺህ 500 ሜትር የሴቶች ሩጫ ውድድር አትሌት ድርቤ ወልተጂ በ3 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ ከ25 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት ቀዳሚ ሆና በመግባት አሸንፋለች።
በውድድሩ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉም በ3 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ ከ48 ማይኮሮ ሰከንድ 2ኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን መረጃ ያመላክታል።