የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጪው ሰኔ 1 ጀምሮ ወደ አክሱም ዳግም በረራ ይጀምራል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመጪው ሰኔ 1 ጀምሮ ወደ አክሱም ዳግም በረራ ይጀምራል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2016(ኢዜአ)፦ ከመጪው ሰኔ 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ዳግም በረራ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ገለጸ።
የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ፤ አየር መንገዱ ወደ አክሱም ዳግም በረራ ለመጀመር የሚያስችሉትን ቅድመ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል።
ይህንንም ተከትሎ ከመጪው ሰኔ 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ ታሪካዊ የቱሪዝም መዳረሻ ወደሆነችው አክሱም ከተማ ዳግም በረራ እንደሚጀመር ነው ኃላፊው የገለጹት።
በረራው መጀመሩ ዓለም አቀፍ ቱሪስቶችና የአገር ውስጥ ጎብኚዎች ወደ ሥፍራው የሚያደርጉትን ጉዞ ለማሳለጥ ያስችላል ብለዋል።
በረራው በሣምንት ሰባት ጊዜ ወደ ሥፍራው የሚደረግ መሆኑንም ጠቁመዋል።
አየር መንገዱ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በረራውን በቀን ወደ 3 እንደሚያሳድግም ገልጸዋል።