ቀጥታ፡

በ25ተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስና ሀዲያ ሆሳዕና በአቻ ውጤት ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 10/2016 (ኢዜአ)፦በ25ተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስና ሀዲያ ሆሳዕና አንድ በአቻ ውጤት ተለያዩ ።

በሐዋሳ ዩንቨርስቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ለሀዲያ ሆሳዕና ዑመድ ኡክሪ ለቅዱስ ጊዮርጊስ በረከት ወልዴ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተክትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ40 ነጥብ 5ተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሀዲያ ሆሳዕና በ35 ነጥብ 8ተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

በሌላኛው የ25ተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ መርሐ ግብር 12 ሰዓት ላይ መቻል ከሐዋሳ ከተማ ጋር ይጫወታሉ።

ትናንት በተደረጉ የ25ኛ ሳምንት የሁለተኛ  ቀን ጨዋታዎች፤ ኢትዮጵያ መድህን  ድሬደዋ ከተማን 5 ለ 0፤ ባህርዳር ከተማ ሀምበሪቾን 2 ለ 0 አሸንፈዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም