ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንን የስራ እንቅስቃሴ እየጎበኘ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣንን የስራ እንቅስቃሴ እየጎበኘ ነው
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 9/2016(ኢዜአ):- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የስራ እንቅስቃሴ እየጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ የምክር ቤቱ አፈ- ጉባኤ ታገሰ ጫፎን ጨምሮ ምክትል አፈ- ጉባኤ ሎሚ በዶ፣ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢና አባላት ተገኝተዋል።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር መሃመድ እድሪስና የስራ ሃላፊዎች የተቋሙን የስራ እንቅስቃሴ ላይ ገለፃ አድርገዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ መሃመድ እድሪስ እንዳሉት፤ የህዝብ መገናኛ ብዙሃን የህብረተሰቡን ባህልና እሴት በማይቃረን መልኩ እንዲሰሩ በቴክኖሎጂ የታገዘ የክትትል ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የሀሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግሮችን ለመከላከል ከህዝብ የሚመጡ ቅሬታዎችን በመለየት መፍትሄ እንዲያገኙ እየተሰራ ነው ብለዋል።
መገናኛ ብዙሃን ማህበረሰብን የመቅረፅ ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ከስልጠና ጀምሮ የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑንም አቶ መሃመድ አብራርተዋል።
ባለስልጣኑ የመገናኛ ብዙሃን ፍቃድን ጨምሮ ከ18 በላይ አገልግሎቶችን በኢ- ሰርቪስ እየሰጠ መሆኑም በጉብኝቱ ጊዜ ተጠቅሷል።