ቀጥታ፡

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ለ42ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎች በማስመረቅ ላይ ይገኛል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 09/2016 (ኢዜአ) የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል ለ42ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ኮማንዶዎች በደማቅ ወታደራዊ ስነ ስርዓት በማስመረቅ ላይ ይገኛል። 

በምረቃ ዝግጅቱ ላይ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላን ጨምሮ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ የጦር ሀይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤሄል ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች፣ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። 


 

ተመራቂዎቹ ኢትዮጵያ የሚል ስያሜ የተሰጣቸውና ከመከላከያ ሠራዊቱ ፣ ከባህር ሀይልና ከፌዴራል ፖሊስ የተውጣጡና ለረጅም ወራት የሰለጠኑ የኮማንዶ አባላት መሆናቸው ታውቋል። 

በዝግጅቱ ላይ ተመራቂዎች የተለያዩ ወታደራዊ ትዕይንት ያሳዩ ሲሆን በእለቱ የክብር እንግዳና በኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች ንግግር ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም