ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወላይታ ድቻን 5 ለ 0 አሸነፈ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 8/2016(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወላይታ ድቻን 5 ለ 0  በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ25ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ወላይታ ድቻን አገናኝቷል።

በዚህ ጨዋታም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወላይታ ድቻን 5 ለ 0  በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል። 

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ፍጹም ግርማ በራሱ ግብ ላይ፣ ጋናዊው ባሲሩ ኡመር፣ ዩጋንዳዊው ሳይመን ፒተር፣ ኤፍሬም ታምራትና ኪቲካ ጅማ ለንግድ ባንክ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ53 ነጥብ የሊጉን መሪነት ማጠናከር ችሏል።

በአንጻሩ ወላይታ ድቻ በ28 ነጥብ ከነበረበት 12ኛ ደረጃ ወደ 13ኛ ዝቅ ብሏል።

በዚሁ መርሃ ግብር ፋሲል ከነማ እና ወልቂጤ ከተማ ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ የሚጫወቱ ይሆናል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም