ተቀማጭነቱን ካርቱም ያደረገው ቀጣናዊ የደህንነት ኦፕሬሽን ማዕከል /ሮክ/ በአዲስ አበባ ውይይት አካሄደ - ኢዜአ አማርኛ
ተቀማጭነቱን ካርቱም ያደረገው ቀጣናዊ የደህንነት ኦፕሬሽን ማዕከል /ሮክ/ በአዲስ አበባ ውይይት አካሄደ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2016(ኢዜአ)፦ ተቀማጭነቱን ካርቱም ያደረገው ቀጣናዊ የደህንነት ኦፕሬሽን ማዕከል(Regional Operational Centre Khartoum) ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አድርጓል።
በአፍሪካ ሕብረት ሥር የተቋቋመው ቀጣናዊ የደህንነት ኦፕሬሽን ማዕከል /ሮክ/ በአዲስ አበባ የመከረው ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን መከላከል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ነው።
በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል፣ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ዘላለም መንግስቴ፣ የቀጣናዊ የደህንነት ኦፕሬሽን ማዕከል /ሮክ/ አባል አገራት ተወካዮች እንዲሁም የኢንተርፖል እና ዩሮ ፖል ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
ቀጣናዊ የደህንነት ኦፕሬሽን ማዕከል /ሮክ/ በአፍሪካ ሕብረት ሥር የተቋቋመ ሲሆን በአውሮፓ ሕብረትም ድጋፍ ይደረግለታል።
የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለመከላከል በትብብር የሚሰሩበት ተቋም መሆኑም ይታወቃል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ አገራት አባል የሆኑበት ሮክ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከልና ለመዋጋት አይነተኛ ሚና እየተወጣ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።