ቀጥታ፡

የተቀናጀ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓትን ለመፍጠር የሚያስችል ሥምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2016(ኢዜአ)፦የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የተቀናጀ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓትን ለመዘርጋት  የሚያስችል ሥምምነት ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ተፈራርሟል። 

ሥምምነቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር አቶ ገብረመስቀል ጫላ ከተቋማቱ አመራሮች ጋር ተፈራርመዋል። 

ተቋማቱም የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣ የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራምና የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ናቸው።

ሥምምነቱ  የአገልግሎት አሰጣጡን ዲጂታል በማድረግ በተቋማት መካከል የተቀናጀ የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል። 

ይህም ለተገልጋዮች የተቀላጠፈና ግልፅ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚያስችል ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም