ቀጥታ፡

ለሀገራዊ የምክክር ሂደቱ መሳካት አስፈላጊውን እገዛና ትብብር የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 7/2016(ኢዜአ)፦ ለሀገራዊ የምክክር ሂደቱ መሳካት አስፈላጊውን እገዛና ትብብር የማድረግ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ገለጸ።

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የምክክር ሂደቱ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ እስካሁን ሲያበረክት የቆየውን አስተዋጽኦ በማስመልከት ውይይት እያደረገ ይገኛል።

ከዚሁ መድረክ በተጓዳኝም ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የተሰበሰቡና ድርጅቶቹን የሚወክሉ አጀንዳዎች ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እንደሚያስረክቡ ተጠቁሟል።


 

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ተወካይ ዋና ዳይሬክተር ሃና ወልደገብርኤል፤ ምክር ቤቱ ወሳኝ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የራሱን አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በተለይም በሰላም ግንባታ፣ በሰብዓዊ ድጋፍ እና ለሀገራዊ ምክክር ሂደት ስኬት የበኩሉን በማበርከት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።

በመሆኑም ለሀገራዊ ምክክሩ መሳካት የምክር ቤቱ ድጋፍና አስተዋጽኦ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል።

በዛሬው ዕለትም ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የተሰበሰቡ እና ድርጅቶቹን የሚወክሉ አጀንዳዎች ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እንደሚያስረክቡ ጠቁመዋል።

በውይይት መድረኩ የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ተወካዮች እና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም