የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቡርኪና ፋሶ ኦጋዱጉ የሚያደርገውን በረራ አሳደገ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቡርኪና ፋሶ ኦጋዱጉ የሚያደርገውን በረራ አሳደገ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቡርኪና ፋሶ ኦጋዱጉ የሚያደርገውን በረራ ወደ ዕለታዊ ማሳደጉን አስታወቀ።
ከግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በረራውን ዕለታዊ በማድረግ ቀልጣፋ የበረራ አማራጭ መፍጠሩንም አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ገልጿል።