የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በሰሜን ሸዋ ዞን ቡልጋ ከተማ ኢንዱስትሪዎችን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በሰሜን ሸዋ ዞን ቡልጋ ከተማ ኢንዱስትሪዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2016(ኢዜአ)፦ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በሰሜን ሸዋ ዞን ቡልጋ ከተማ አሥተዳደር የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
ከጉብኝቱ ጎን ለጎን የተለያዩ ፋብሪካዎችን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።
የሰሜን ሸዋ አሥተዳደርም የኢትዮጵያ ታምርት አካል የሆነ የኢንቨስትመንት ፎረም እያካሄደ ነው።
በኢንቨስትመንት ፎረሙ ላይ የተለያዩ ባለሃብቶች እና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ መሆናቸውን አሚኮ ዘግቧል።
ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የሥራ እንቅስቃሴ በፋብሪካዎች እና በኢትዮጵያ ታምርት ኤግዚብሽን ላይ ምልከታ አድርገዋል።
በፕሮግራሙ ላይ አጠቃላይ የሰሜን ሸዋ የኢንቨስትመንት ጸጋዎች፣ የልማት እና አገልግሎት ሁኔታ እና ቀጣይ እድሎች ላይ ምክክር ይካሄዳል።
በቀጣናው ኢንቨስትመንት ከፍተኛ ድርሻ ላላቸው አካላትም እውቅና ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
በመድረኩ ላይ ከፍተኛ የክልል እና የዞኑ አመራሮችም ተገኝተዋል።