ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እንድታመርት ብቻ ሳይሆን ያመረተችውን እንድትጠቀም መንግስት ትልቅ ትኩረት ሰጥቷል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እንድታመርት ብቻ ሳይሆን ያመረተችውን እንድትጠቀም መንግስት ትልቅ ትኩረት ሰጥቷል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ትላንት ለሁለተኛ ጊዜ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ማጠናቀቂያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ታድመናል ብለዋል፡፡


 

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዓላማው ሁለት ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመጀመሪያው እንደ ሀገር ያሉንን የልማት ዕድሎች እጅግ በተሻለ መንገድ መጠቀም መሆኑን ገልጸዋል።

ሁለተኛውን ሲያክሉም ዘርፉ በሚፈለገው ልክ እንዳያድግ ያደረጉ ማነቆዎችን በቅንጅት መፍታት መቻል ነው ብለዋል።


 

መንግስት ለዘርፉ ዕድገት ልዩ ትኩረት በመስጠት ኢትዮጵያ እንድታመርት ብቻ ሳይሆን ያመረተችውን እንድትጠቀምም ትልቅ ትኩረት ሰጥቷል ሲሉም ገልጸዋል በመልዕክታቸው፡፡

መላው የኢትዮጵያ ህዝብም የሀገር ውስጥ ምርትን የመጠቀም ባህልን እንዲያጎለብት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም