የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄን ተቀላቀለ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄን ተቀላቀለ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ለ#ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄን 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በማድረግ ተቀላቅሏል።
ንቅናቄው አካባቢያችንን ጽዱ፣ ውብ እና ለመኖሪያ ምቹ ለማድረግ ከማስቻሉም በላይ የተሻለ ካባቢን ለትውልድ ለማስተላለፍ የሚያስችል በመሆኑ ኮርፖሬሽኑ ባደረገው ድጋፍ ከፍተኛ ደስታ እንደሚሰማው አስታውቋል።