ኢ ሲ ደብሊው ሲ - ሀውሲንግ ደቨሎፕመንት ኦፊስ ኮንትሮል ኤ ለ #ጽዱኢትዮጵያ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
ኢ ሲ ደብሊው ሲ - ሀውሲንግ ደቨሎፕመንት ኦፊስ ኮንትሮል ኤ ለ #ጽዱኢትዮጵያ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2016(ኢዜአ)፦ኢ ሲ ደብሊው ሲ - ሀውሲንግ ደቨሎፕመንት ኦፊስ ኮንትሮል ኤ ለ #ጽዱኢትዮጵያ ንቅናቄ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ።
ለጽዱ ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 50 ሚሊየን ብር የማሰባሰብ የዲጂታል ቴሌቶን ከማለዳው ሁለት ሰአት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በንቅናቄውም ኢ ሲ ደብሌው ሲ - ሀውሲንግ ደቨሎፕመንት ኦፊስ ኮንትሮል ኤ ለ #ጽዱኢትዮጵያ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለግሷል።
ከማለዳው ጀምሮ የዲጂታል ቴሌቶኑ በጠንካራ ተሳትፎ እንደቀጠለ ነው።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248፣ በብሔራዊ ባንክ የዶላር አካውንት 0101211300016 እና በስዊፍት ኮድ NBETETAA የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄ እንዲቀላቀልም ጥሪ ቀርቧል፡፡