የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ለጽዱ ኢትዮጵያ ዲጂታል ቴሌቶን 8 ሚሊዮን ብር ለገሰ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ለጽዱ ኢትዮጵያ ዲጂታል ቴሌቶን 8 ሚሊዮን ብር ለገሰ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ለጽዱ ኢትዮጵያ ዲጂታል ቴሌቶን 8 ሚሊዮን ብር ለገሰ፡፡
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሜቴ፣ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች እንዲሁም የአትሌቲክስ እና የእግር ኳስ ደጋፊዎች የጽዱ ኢትዮጵያ ዲጂታል ቴሌቶንን ተቀላቅለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ የኦሊምፒክ ኮሚቴው 5 ሚሊዮን ብር እንዲሁም በግላቸው 3 ሚሊዮን ብር፤ በድምሩ 8 ሚሊዮን ብር ለግሰዋል፡፡
በተጨማሪ አትሌቶች፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስና እግር ኳስ ደጋፊዎች፣ የቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች በጋራ በመሆን ንቅናቄውን ተቀላቅለዋል፡፡
ህብረተሰቡ ብሎም ተቋማት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248፣ በብሔራዊ ባንክ የዶላር አካውንት 0101211300016 እና በስዊፍት ኮድ NBETETAA የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄ በመቀላቀል አሻራቸውን እንዲያሳርፉ ጥሪ ቀርቧል፡፡