ቀጥታ፡

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የጽዱ ኢትዮጵያ ዲጂታል ቴሌቶንን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የጽዱ ኢትዮጵያ ዲጂታል ቴሌቶንን ተቀላቀሉ፡፡

በንቅናቄው ከአትሌቶች በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እንዲሁም የአትሌቲክስ እና የእግር ኳስ ደጋፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተቀላቅለዋል፡፡

ለጽዱ ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 50 ሚሊየን ብር የማሰባሰብ የዲጂታል ቴሌቶን ከማለዳው ሁለት ሰአት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ሲሆን፤ በተለያዩ የሙያ መስኮች የሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ንቅናቄውን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።

ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ ስሟን ከፍ አድርገው ያስጠሩ አትሌቶችም ንቅናቄውን በማቀላቀል አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት አሸብር ወልደጊዮርጊስ(ዶ/ር)፤ ንቅናቄው ጽዱ አካባቢን ከመፍጠር ባሻገር ለአትሌቲክስ ልምምድ ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያን ጽዱ ማድረግ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ስራ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህ በጎ ተግባር ሁሉም የበኩሉን ድጋፍ ሊያደርግ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በንቅናቄው ከተሳተፉ አትሌቶች መካከል አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በበኩሏ ንቅናቄው ኢትዮጵያን የሚለውጥ በመሆኑ ሁሉም ሊሳተፍ እንደሚገባ ተናግራለች፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም