ዛሬ የተመረቀው የአባይ ድልድይ በሰዎች መካከል ያለን ግንኙነት በማጠናከር እና የንግድ እድሎችን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ርምጃ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) - ኢዜአ አማርኛ
ዛሬ የተመረቀው የአባይ ድልድይ በሰዎች መካከል ያለን ግንኙነት በማጠናከር እና የንግድ እድሎችን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ርምጃ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 4/2016(ኢዜአ)፦ ዛሬ በባህርዳር ከተማ የተመረቀው የአባይ ድልድይ በሰዎች መካከል ያለን ግንኙነት በማጠናከር እና የንግድ እድሎችን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ርምጃ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከግዘፋዊ ቁሳዊ መዋቀሩ ባሻገርም ልዩነቶችን የማጥበብ፤ በተቃራኒ ጎራ ላሉ ሰዎች መገናኛ ድልድዮችን የማነፅ ርዕያችን መዘርጊያ ምልክት ነው ሲሉም አክለዋል።
ኅብረታዊ ምሉዕነትን ለማፅናት ከክልላዊ ወሰኖች የሚሻገር ትርክት የመቅረፅ ትልማ ማሳያ ነውም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመዕልክታቸው።
ግባችን በክልከላ እና ቁንፅልነት የሚመሩ የአእምሮ ውቅሮች እና ትርክቶችን በማስወገድ በሁሉም ዘንድ ትብብርን እና አንድነት ማሳደግ ነው ብለዋል።