ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የፕሪሚየር ሊጉን መሪነት ያጠናከረበት ድል አስመዝግቧል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2016(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ24ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልቂጤ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል።

በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ማምሻውን በተካሄደው ጨዋታ ተከላካዩ ሱሌማን ሀሚድ በ25ኛው እና የአማካይ ተጫዋቹ ፉአድ ፈረጃ በ48ኛው ደቂቃ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማሸነፊያ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

የአማካይ ተጫዋቹ ሳምሶን ጥላሁን በ89ኛው ደቂቃ ለወልቂጤ ከተማ ብቸኛዋን ግብ አስቆጥሯል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ50 ነጥብ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል።

ወልቂጤ ከተማ በ16 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ቀን ላይ በተደረገ የ24ኛ ሳምንት ጨዋታ ኢትዮጵያ መድን ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸንፏል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም