ቀጥታ፡

የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አሥፈጻሚ አባላት ባሕር ዳር ገቡ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2016(ኢዜአ)፦ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አሥፈጻሚ አባላት ባሕር ዳር ከተማ ገብተዋል።

ከአባላቱ ውስጥ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ የክልሎች ርእሳነ መሥተዳድሮች፣ ሚኒስትሮች እና ሌሎችም ይገኙበታል።



 

አባላቱ በባሕር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ሌሎችም የከተማው ነዋሪዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የክልሎች ርእሳነ መሥተዳድሮች እና ሌሎችም የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አሥፈጻሚ አባላት በአማራ ክልል በሚኖራቸው ቆይታ በክልሉ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን ይመለከታሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አሚኮ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም