ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ኬንያ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ ፤ ግንቦት 2/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በፊፋ ሴቶች ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ከኬንያ ጋር ባደረገው ጨዋታ ያለ ምንም ግብ አቻ ወጥቷል።

ሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የመልስ ጨዋታቸውን ግንቦት 11 ቀን 2016 ዓ.ም በናይሮቢ ያደርጋሉ።

በደርሶ መልስ የሚያሸንፈው ቡድን በመጨረሻው የማጣሪያ ዙር ከጅቡቲና ብሩንዲ አሸናፊ ጋር ይጫወታል።

በዶሚኒካን ሪፐብሊክ አስተናጋጅነት በጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም በሚካሄደው ስምንተኛው የፊፋ ሴቶች ከ17 ዓመት በታች የዓለም ዋንጫ 16 አገራት ይሳተፋሉ።

አፍሪካም በዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) የሶስት አገራት ተሳትፎ ኮታ ተሰጥቷታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም