የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክን የተመለከተ የፓናል ውይይት በቦንጋ ከተማ መካሄድ ጀመረ - ኢዜአ አማርኛ
የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክን የተመለከተ የፓናል ውይይት በቦንጋ ከተማ መካሄድ ጀመረ
ቦንጋ፤ ግንቦት 2/2016 (ኢዜአ)-የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክን በማስመልከት የተዘጋጀ የፓናል ውይይት በቦንጋ ከተማ መካሄድ ጀመረ።
የክልሉ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ምክትል ሃላፊና የስፖርት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አህመዲን አወል እንዳሉት በፖናል ውይይቱ ላይ የክልሉን የአትሌቲክስ አቅምና ያሉ ፈተናዎች ላይ በጋራ ይመክራል።
ለቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ተለይተው እንደሚቀመጡም አመልክተዋል።
ከእዚህ በተጨማሪ በሀገር አቀፍ የኦሎምቲክ ውድድር ላይ የክልሉ ተሳትፎ እንዲሁም ክልሉ በቀጣይ በዘርፉ ውጤታማ ሥራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረት ውይይት እንደሚደረግ አቶ አህመዲን አመልክተዋል።
በውይይቱ ላይ ለመሳተፍ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉና የኦሎምፒክ ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባላትና ታዋቂ ስፖርተኞች ተገኝተዋል።
በነገው ዕለትም የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ ችቦ አቀባበልና ሽኝት መርሃ-ግብር የሚካሄድ ሲሆን የአጭር ርቀት ሩጫ፣ የብስክሌት ውድድር እና ሌሎች ኩነቶችም እንደሚካሄዱ ታውቋል።