ቀጥታ፡

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አመራሮች እና ሰራተኞች የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2016(ኢዜአ)፦ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አመራሮች እና ሰራተኞች ለጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የ134 ሺህ ብር ድጋፍ አደረጉ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ ለሆነው የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ኤምባሲው በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳሰፈረው የኤምባሲው አመራርና ሰራተኞች ለ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄ የ134 ሺህ ብር ድጋፍ በማድረግ ንቅናቄውን ተቀላቅለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም