ቀጥታ፡

የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የመስመር ማዛወር ስራ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2016(ኢዜአ)፡- የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሪደር ልማት የኤሌክትሪክ መስመር ማዛወር እና መልሶ ግንባታ ስራ አጠናቆ ለደንበኞች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

በመስመር ማዛወር ስራው ወቅት የልማት ተነሺ ለነበሩ 2 ሺህ 700 ደንበኞች አዲስ ኃይል የማገናኘት ስራ መከናወኑን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኃይል መስመር ማዛወር ስራው አጠቃላይ 68 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን፤ በቀጣይ የኃይል መቆራረጡን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ ታሳቢ በማድረግ 50 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ እና 18 ኪሎ ሜትር የዝቅተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ ማሻሻያ ተደርጓል ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም