የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ትሩፋቶቹና የተሸጋገሩ እዳዎች ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 1/2016(ኢዜአ)፡- በ50 ዓመታት የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ትሩፋቶቹና የተሻገሩ እዳዎች ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው አራተኛው ልዩ አውደ ጥናት የኢትዮጵያ አብዮት ከ50 ዓመት በኋላ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ትሩፋቶቹና የተሸጋገሩ እዳዎች በሚል ርዕስ ነው እየተካሄደ ያለው።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ(ዶር)፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሀገራዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ መድረኮችን እያካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።


 

የውይይት መድረኮቹ ለፖሊሲ ግብአትና ለሀገራዊ ሁለንተናዊ ልማትና አድገት የላቀ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑንም ጠቅሰዋል። 

በዩኒቨርሲቲው አስተባባሪነት ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ፣ በሀገራዊ ምክክር ተሞክሮና ጠቀሜታ፣ የአድዋ ድል እንድምታ ላይ መድረኮች መካሄዳቸውን አስታውሰዋል።

በዛሬው እለት ደግሞ በ50 ዓመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ትሩፋቶቹና የተሸጋገሩ እዳዎች በሚል ርዕስ አራተኛውን ልዩ አውደ ጥናት እያካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።

በመድረኩ ምሁራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም