የፌዴራልና የክልል የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጎንደር ከተማ ገቡ

ጎንደር፣ ሚያዝያ 30/2016(ኢዜአ)፦ የብልፅግና ፓርቲ የዋናው ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መለስ አለሙ ፣ የብልፅግና ፓርቲ የዋናው ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ፖል ቱትና የአማራ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ግርማ መለሰ ጎንደር ከተማ ገብተዋል።

ጎንደር አፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩህ አቡሃይን ጨምሮ ሌሎች የከተማው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በነገው ዕለትም የብልፅግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ የ9 ወር ግምገማና በቀጣይ አቅጣጫ ዙሪያ የውይይት መድረክ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም