ከቤንዚል ውጪ ያሉ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል ተወሰነ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 30/2016(ኢዜአ)፡- ከቤንዚል ውጪ ያሉ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መረጃ በአለም ገበያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየታየ የመጣውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ መነሻ በማድረግ በቤንዚን የችርቻሮ መሸጫ ላይ ብቻ መጠነኛ ማሻሻያ ተደርጓል ብሏል።

ከግንቦት 1/2016 ከምሽቱ 6 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ ያለው የነጭ ናፍጣ፣ የኬሮሲን፣ የአይሮፕላን ነዳጅ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑንም አስታውቋል።

የቤንዚን የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ የተደረገ መጠነኛ ማስተካከያ ተደርጓል።

በዚህም :-

ቤንዚን ……………………………………… ብር 78 ከ67 በሊትር

ነጭ ናፍጣ…………………………………… ብር 79 ከ75 በሊትር

ኬሮሲን ……………………………………... ብር 79 ከ75 በሊትር

የአውሮፕላን ነዳጅ …………………………... ብር 70 ከ83 በሊትር

ቀላል ጥቁር ናፍጣ…………………………… ብር 62 ከ36 በሊትር

ከባድ ጥቁር ናፍጣ……………………………. ብር 61 ከ16 በሊትር መሆኑንም ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም