የጤና እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴሮች የ2017 የበጀት ስሚ መርሀ-ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 30/2016(ኢዜአ)፡- አራተኛ ቀኑን በያዘው የፌዴራል ባለበጀት መስሪያ ቤቶች የበጀት ስሚ መርሀ-ግብር የጤና እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴሮች እንዲሁም የተጠሪ ተቋማት የ2017 የበጀት ዕቅድ ለገንዘብ ሚኒስቴር ቀርቦ ተገምግሟል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የበጀት ስሚ መርሀ-ግብሩን በከፈቱበት ወቅት የጤና ጉዳይ የተለየ ትኩረት የሚሻ ቢሆንም በጀት የፖሊሲ ማስፈጸሚያ በመሆኑ የሚቀርቡ የበጀት ጥያቄዎች የአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል የሆነውን የ2016-2018 ዓ.ም የልማትና የኢንቨስትመንት ዕቅድ ግቦችን ከማስፈጸም አኳያ የተቃኘ ሊሆን እንደሚገባው አመልክተዋል፡፡


 

በተመሳሳይ መልኩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዕቅድም ቀርቦ ተገምግሟል፡፡

በሁለቱም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የበጀት ዕቅድ ላይ ዝርዝር ግምገማ ከተካሄደ በኋላ ከገንዘብ ሚኒስቴር የተለያዩ የሥራ ክፍሎች ሙያዊ የማስተካከያ ሀሳቦችና አስተያየቶች መቅረባቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የጤና እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሮች የቀረቡላቸውን ዝርዝር አስተያየቶችንና ምክረ-ሃሳቦችን በግብዓትነት አካተው በተቀመጠው የበጀት ጣራ መሠረት፣ ቁጠባና ውጤታማነትን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የተስተካከለ የበጀት ዕቅዳቸውን በጥቂት ቀናት ውስጥ ለገንዘብ ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ አቅጣጫ መሰጠቱም ተጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም