በገንዳ ውኃና ደሴ ከተሞች የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ አቅም ለሌላቸው ወገኖች ማዕድ የማጋራት ስነ ስርዓት

መተማ፤ ደሴ ፤ ሚዚያ 27/2016 (ኢዜአ)፡- በገንዳ ውኃና ደሴ ከተሞች የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ አነሰተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች የማዕድ ማጋራት ስነ-ስርዓት ተከናወነ።

በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውሃ ከተማ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ320  አነስተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች ማዕድ ማጋራታቸው ተገልጿል።

የገንዳ ውሃ ከተማ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሂሩት ጌትነት እንዳሉት፤ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ከህብረተሰቡና ከተቋማት ባሰባሰቡት 400 ሺህ ብር የእርድ እንስሳት በመግዛት ማዕድ አጋርተዋል።

ማዕድ ካጋሩ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች መካከል ወጣት ፈንታሁን አስማረ፤ መደጋገፍን ባህል በማድረጋቸው አቅም የሌላቸውን እየደገፉ መሆኑን ተናግሯል።

አቶ መልካሙ መኮንን፤ በወጣቶቹ ተነሳሽነት በተደረገላቸው ማዕድ ማጋራት  በዓሉን በደስታ ማዋል እንደቻሉ ገልፀዋል።

በተመሳሳይ በደሴ ከተማ የ'አውራምባ ጥምረት በጎ ፍቃደኞች ማህበር' ለትንሳኤ በዓል ለአረጋዊያንና አካል ጉዳተኞች ማዕድ የማጋራት መርሃ ግብር መከናወኑን የገለፁት የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ምስክር ሰይድ ናቸው።

ማህበሩ ከ150 ለሚበልጡ አቅመ ደካሞች የምሳ ግብዣ ማደረጉን ገልጸዋል።

ማዕድ ከተጋሩት መካከል ወይዘሮ ፋጤ ሰይድ በበኩላቸው፤ በዓሉን በደስታና በጋራ ከማሳለፋቸውም ባለፈ የአልባሳት ድጋፍ እንደተደረገላቸው አስታውቀዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም