የኢትዮጵያን የአብሮነት፣ የመደጋገፍና ተካፍሎ የመብላት እሴቶችን ጠብቀን ልንቀጥል ይገባል- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 27/2016(ኢዜአ)፡- የኢትዮጵያን የአብሮነት፣ የመደጋገፍ፣ የፍቅር፣ የመተዛዘንና ተካፍሎ የመብላት እሴቶች ጠብቀን ልንቀጥል ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ማለዳ አብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ማዕድ አጋርተዋል።


 

በዚሁ መርሃ-ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክትም፤ በዓሉን ስናከብር እርስ በርሳችን በመዋደድ፣ በመረዳዳትና በመደጋገፍ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።


 

የኢትዮጵያን የአብሮነት፣ የመደጋገፍ፣ የፍቅር፣ የመተዛዘንና ተካፍሎ የመብላት እሴቶች ጠብቀን ልንቀጥል ይገባልም ብለዋል።

የአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ውብአየሁ ማሞ፤ የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመተባበር ከ200 ለሚልቁ ሰዎች ማዕድ አጋርተናል ብለዋል።


 

የማዕድ ማጋራቱ ዓላማም ለወገኖቻችን ያለንን ፍቅር፣ አብሮነትና አጋርነት ለማሳየት ነው ሲሉ ተናግረዋል።

በማዕድ ማጋራት ላይ የተገኙትም ለተደረገላቸው ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመላ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዝግጅቶች በመከበር ላይ ይገኛል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም