ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 27/2016(ኢዜአ)፡- የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

በመልዕክታቸውም በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ የሚከበረው የትንሳኤ በዓል የሰላም፣ የአንድነት፣ የደስታ እና የመተሳሰብ እንዲሆን ተመኝተዋል።

የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን ሲያከብሩ ሃይማኖታቸው በሚያዘው መሠረት እያከበሩ የተቸገሩትን በመርዳት ማህበራዊ ግንኘነትን ማጠናከር ያስፈልጋል ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም