የአፍሪካ ሕብረት ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ

አዲስ አበባ፤ ሚያዚያ 27/2016(ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ሕብረት የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

የሕብረቱ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ ሰላምና ደህንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ፤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ለኢትዮጵያዊያን የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።


 

የትንሳኤ በዓል አዲስ ተስፋን የሚፈነጥቅ የበረከትና የፍቅር እንዲሆንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል።


 

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሳችሁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላለፈዋል።

በትናንትናው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የሃይማኖት መሪዎች በተመሳሳይ መልእክታቸውን ማስተላለፋቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም