የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 27 /2016(ኢዜአ)፦የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ የተነሳበት ዕለት የሚታወስበት ነው።

የትንሳኤ በዓልን አስመልክቶ የሃይማኖት አባቶች ባስተላለፉት መልዕክት በዓሉን ስናከብር ለሰው ልጆች ሁሉ ሰላምና ደህንነት በመጸለይና የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል።

በዓለ ትንሳኤው ሲከበር ለእግዚአብሄር ክብርና ለሰው ልጆች ደኀንነት በአንድነት በመቆም መሆን እንዳለበትም አመልክተዋል።

በመሆኑም የትንሳኤ በዓል በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ዝግጅቶች በመላው ኢትዮጵያ እየተከበረ ይገኛል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም